የተሻለ ክህሎትና የተሻለ የትምህርት ደረጃ በሙያ መስክዎም ሆነ በሕይወትዎ የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ሊረዳዎ ይችላል። በአካባቢዎ ማኅበረሰብ ወይም የሞያ ኮሌጅ የብሩህ ተስፋ ጉዞዎን ይጀምሩ።.
የሙያና የትምህርት ጎዳናዎች
የሙያ ወይም የትምህርት ጎዳናዎችን መከተል ማለት ተጨማሪ ትምህርት በመከታተል ወደተሻለ ሥራ መሸጋገር ይችላሉ ማለት ነው። በጎዳናው ላይ ያለ እያንዳንዱ እርምጃ ወደ ቀጣዩ የሥራ እርከንና ክፍያ እንዲደርሱ ይረዳዎታል።
ለከፍተኛ ደረጃ ትምህርትም ራስዎን ሊያዘጋጁ ይችላሉ።
ለምሳሌ ያህል ነርስ መሆን የሚፈልጉ ከሆነ በመጀመሪያ የCNA (ፈቃድ ያለው ረዳት ነርስ (Certified Nursing Assistant)) ሰርተፍኬትዎን ሊይዙ ይችላሉ። ትንሽ ከሠሩ በኋላ ደግሞ ወደ ትምህርት ቤት ተመልሰው የLPN (ፈቃድ ያለው ፕራክቲካል ነርስ (Licensed Practical Nurse)) ዲግሪዎን ሊይዙ ይችላሉ። ከዚያም የRN (የተመዘገበ ነርስ (Registered Nurse)) ዲግሪዎን ሊይዙ ይችላሉ። ከጊዜ በኋላ የዩኒቨርሲቲ የነርሲንግ ዲግሪ መያዝ ይፈልጉ ይሆናል።
ለእድሜ ልክ የሚጠቅም ትምህርት
ኢኮኖሚውና ዓለም አቀፉ የሥራ ሁኔታ በፍጥነት ይለዋወጣል። ከለውጦቹ ጋር እኩል ለመራመድ ዛሬ ያሉ ሠራተኞች ለዘለቄታው ለሥራ ሕይወታቸው የሚጠቅም ክህሎት ማዳበር ያስፈልጋቸዋል። ይህም ጥቂት የኮምፒውተር ሥልጠናዎች መውሰድ ወይም የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ መያዝ ሊጠይቅ ይችላል።
እንዲያውም የማኅበረሰብና የሙያ ኮሌጅ ተማሪ የሆኑት አዋቂዎች ዲግሪ ያላቸው ሰዎች ናቸው። እነዚህ ተማሪዎች አዳዲስ ባለሙያዎችን ለማሰልጠን ወደ ማኅበረሰቡ ኮሌጆች ተመልሰው ይመጣሉ።
ተጨማሪ ትምህርት በመከታተል ገቢዎን ምን ያህል ማሳደግ ይችላሉ?
| የትምህርት ደረጃ |
አማካይ ዓመታዊ ክፍያ |
| ምንጭ፦ U.S. Census Bureau, Educational Attainment in the United States: 2006, Table 8: Year Round Full-Time Workers. http://www.census.gov/population/www/socdemo/education/cps2006.html
|
| ከዩናይትድ ስቴትስ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ዲፕሎማ ያነሰ |
$ 22,326 |
| የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ዲፕሎማ ወይም GED |
$ 31,209 |
| አሶሲየት ወይም የሙያ ዲግሪ/ሰርተፍኬት |
$ 40,708 |
| ባችለር ዲግሪ |
$ 51,436 |
| ማስተርስ ዲግሪ |
$ 64,540 |
| ፕሮፌሽናል ዲግሪ |
$ 100,000 |
| ዶክትሬት ዲግሪ |
$ 85,774 |