የማኅበረሰብና የሙያ ኮሌጆች ማንኛውንም ጎልማሳ ተማሪ በደስታ ይቀበላሉ።
ክፍት የትምህርት ዕድል
“ክፍት ዕድል” ሲባል ኮሌጆቹ በሁሉም የትምህርት ደረጃ ላይ ላሉ ሰዎች የትምህርት ክፍሎቻቸውና የተማሪዎች አገልግሎቶቻቸው ክፍት ናቸው ማለት ነው። የምደባ ፈተናዎች እርስዎም ሆኑ ኮሌጁ ለእርስዎ የሚመጥነውን ትምህርት ለመምረጥ ያስችላችኋል።
ኮሌጅ መምረጥ
በአቅራቢያዎ ያለ ኮሌጅ ለማግኘት የኮሌጅ መፈለጊያውን ይጠቀሙ። በቦታ እንዲሁም በትምህርት ፕሮግራሞችም አማካኝት ኮሌጅ መፈለግ ይችላሉ።.
የመረጡትን ኮሌጅ የምዝገባ ደረጃዎች ይከተሉ።
እንደ ጥርስ ንጽህና (ዴንታል ሃይጂን) ወይም ነርሲንግ ያሉት አንዳንድ የዲግሪ ፕሮግራሞች ልዩ የመግቢያ መመዘኛ ወይም ወረፋ ይኖራቸዋል። በተጨማሪም አንዳንድ ተማሪዎች — እንደ ራኒንግ ስታርት ወይም የተማሪ ቨዛ ያላቸው ዓለም አቀፍ ተማሪዎች — የተለያዩ ማመልከቻዎችን እንዲሞሉ ይጠየቃሉ።
I-BEST: ESL ከሥራ ስልጠና ጋር ተጣምሮ የሚሰጥበት
ብዙ ኮሌጆች I-BEST (Integrated Basic Education and Skills Training (የተቀናጀ መሠረታዊ ትምህርትና የክህሎች ስልጠና) የተባለ ፕሮግራም አላቸው። ይህ ፕሮግራም እንግሊዝኛ ሁለተኛ ቋንቋቸው ለሆነ የሚሰጠውን (English as a Second Language (ESL)) ትምህርት ከሥራ ስልጠና ጋር አጣምሮ የያዘ ሲሆን ተማሪዎቹ የእንግሊዝኛ ችሎታቸውንና የሥራ ክህሎታቸውን ጎን ለጎን እንዲያሻሽሉ ይረዳቸዋል።
በተጨማሪም I-BEST የጎልማሶች መሠረታዊ ትምህርትን (Adult Basic Education (ABE)) ከሥራ ስልጠና ጋር አጣምሮ ይዟል። ስለ I-BEST ፕሮግራሞች ለማወቅ በአካባቢዎ የሚገኘውን ኮሌጅ ይጠይቁ።
የኮሌጅ ክፍያ
በአካባቢዎ የሚገኘው ኮሌጅ ብቁ ሆነው የተገኙ ተማሪዎች የኮሌጅ ክፍያቸውን መክፈል የሚችሉባቸውን መንገዶች በማፈላለግ ሊረዳቸው ይችላል። በተማሪዎች አገልግሎት ክፍል ውስጥ ያለ አንድ ሰው ለማነጋገር ይጠይቁ።
ፕሮግራሞቹ የገንዘብ ድጋፍ፣ ስጦታ፣ እየሠሩ መማር የሚቻልበትን ሁኔታ፣ የሠራተኞች ተጨማሪ ስልጠና ፕሮግራም (Worker Retraining program) እና ብድርን ሊያካትቱ ይችላሉ። አልፎ ተርፎም እንደ ቅጥር ሁኔታዎና እንደ ቤተሰብዎ ሁኔታ ታይቶ ልዩ የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘትም ብቁ ሊሆኑ ይችሉ ይሆናል።